unfoldingWord 30 - ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ
概要: Matthew 14:13-21; Mark 6:31-44; Luke 9:10-17; John 6:5-15
文本編號: 1230
語言: Amharic
聽眾: General
類型/流派: Bible Stories & Teac
目的: Evangelism; Teaching
聖經摘錄: Paraphrase
狀態: Approved
腳本是翻譯和錄製成其他語言的基本指南,它們需要根據實際需要而進行調整以適合不同的文化和語言。某些使用術語和概念可能需要有更多的解釋,甚至要完全更換或省略。
文本文字
ኢየሱስ በተለያዩ ብዙ መንደሮች እንዲሰብኩና ሰዎችን እንዲያስተምሩ ሐዋርያቱን ላከ። እነርሱ ኢየሱስ ወደ ነበረበት በተመለሱጊዜ፣ ያደረጉትንነገር ነገሩት።ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሐይቁን ተሻግረውጸጥታ ወዳለበት ቦታ አብረውት እንዲሄዱናጥቂት እንዲያርፉ ጋበዛቸው። ስለዚህጀልባ ውስጥ ገቡና ሐይቁን ተሻገሩ።
ነገር ግን በጀልባውሲሄዱ ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን ያዩአቸው ብዙሰዎች ነበሩ። እነዚህሰዎች ሊቀድሙአቸው በባሕሩዳርቻ ሮጡ። ስለዚህ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ በደረሱጊዜ፣ በጣም ብዙሰዎች አስቀድመውበዚያ ተገኝተው ይጠባበቁአቸው ነበር።
ሕዝቡ ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ከ5000 በላይ ወንዶች ነበሩ። ኢየሱስ ለሕዝቡ እጅግ አዘነላቸው። ለኢየሱስ እነዚህ ሕዝብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ነበሩ። ስለዚህ አስተማራቸውና በመካከላቸው የነበሩትን በሽተኞች ፈወሳቸው።
በዚያ ምሽት ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብለው ነገሩት፣ “ጊዜው መሽቶአልና በአቅራቢያው ከተሞች የሉም። የሚበሉትን ነገር ይገዙ ዘንድ ሕዝቡን አሰናብታቸው።”
ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱን፣ “የሚበሉትን እናንተ ስጡአቸው!” አላቸው። እነርሱም፣“ይህን ማድረግ እንዴት እንችላለን? ያለን አምስት እንጀራናሁለት ዓሣ ብቻ ነው”ብለው መለሱለት።
ሃምሳ ሃምሳ ሆነው ሣሩ ላይ እንዲቀመጡ ለሕዝቡ ይነግሩ ዘንድ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው።
ከዚያም ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመለከተ፣ ስለ ምግቡም እግዚአብሔርን አመሰገነ።
ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ዓሣውን ቈረሰ። ለሕዝቡ እንዲያቀርቡም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። ደቀ መዛሙርቱ ምግቡን ማደላቸውን ቀጠሉ፣ ከቶም አላለቀም! ሕዝቡ ሁሉ በልተው ጠገቡ።
ከዚያ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቊርስራሹን ምግብ ሰበሰቡ፣ እርሱም ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ነበር! ምግቡ ሁሉ የመጣው ከአምስቱ እንጀራና ከሁለቱ ዓሣ ነበር።