unfoldingWord 05 - የተስፋው ልጅ
Esquema: Genesis 16-22
Número de guión: 1205
Lugar: Amharic
Audiencia: General
Propósito: Evangelism; Teaching
Features: Bible Stories; Paraphrase Scripture
Estado: Approved
Los guiones son pautas básicas para la traducción y grabación a otros idiomas. Deben adaptarse según sea necesario para que sean comprendidas y relevantes para cada cultura e idioma diferentes. Algunos términos y conceptos utilizados pueden necesitar más explicación o incluso ser reemplazados o omitidos por completo.
Guión de texto
ከዐሥር ዓመታት በኋላ አብራምና ሦራ ከነዓን ደረሱ፣ እስከዚህ ድረስ ልጅ አልነበራቸውም። ስለዚህም የአብራም ሚስት ሦራ እንዲህ አለችው “እግዚአብሔር ልጆች እንዳይኖሩኝ ስለከለከለኝና እኔም ስላረጀሁ አገልጋዬ አጋር ይህችትልህ አግባት ለኔም ልጅ ትውለድለኝ” አለችው።
ስለሆነም አብራም አጋርን አገባት። አጋርም ወንድ ልጅ ወለደች። አብራምም “እስማኤል” ሲል ስም አወጣለት፤ ይሁን እንጂ ሦራ በአጋር ቀናችባት፤ እስማኤል ዐሥራ ሦስት ዓመት ሲሆነው እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው።
እግዚአብሔርም አብራምን“እኔ ኤልሻዳይ አምላክ ነኝ ካንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ” አለው። አብራምምበግምባሩ መሬት ላይ ተደፋ እግዚአብሔርም አብራምንአለው “አንተ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ። የከነዓንን ምድር ለአንተና ለዘሮችህ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ እኔም ለዘላለም አምላካቸው እሆናለሁ አንተም በቤተ ሰብህ የሚገኘውን ወንድ ሁሉ ግረዘው” አለው።
እግዚአብሔርም “ሚስትህ ሦራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች እርሱም የተስፋው ልጅ ይሆናል ስሙን ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ ኪዳኔንም ከእርሱ ጋር አደርጋለሁ። እርሱም ታላቅ ሕዝብ ይሆናል። እስማኤልንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤ ይሁን እንጂ ኪዳኔ ከይስሐቅ ጋር ይሆናል” አለው። እግዚአብሔርም የአብራምን ስም “አብርሃም” ሲል ለወጠለት ትርጓሜውም “የብዙዎች አባት” ማለት ነው። እግዚአብሔር የሦራንም ስም “ሣራ” ሲል ለወጠላት ትርጓሜውም “የብዙዎች እናት” ማለት ነው።
በዚያኑ ዕለት አብርሃም በቤተ ሰቡ የሚኙትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ። ከዓመት በኋላ አብርሃም 100 ዓመት ሲሆነውና ሣራ 99 ዓመት በሆናት ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት እግዚአብሔርም እንዳላቸው “ይስሐቅ” ሲሉ ስም አወጡለት።
ይስሐቅ ወጣት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት እንዲህ ሲል ፈተነው፤ “አንዱን ልጅህን ውሰድና ለኔ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው፤ እንደ ገና አብርሃም እግዚአብሔርን ታዘዘና ልጁን ሊሠዋው አዘጋጀ።
አብርሃምና ይስሐቅ መሥዋዕት ወደሚደረግበት ስፍራ መጓዝ እንደ ጀመሩ ይስሐቅ አባቱን “አባቴ ሆይ ለመሥዋዕት ማቅረቢያ እንጨቱ ይኸውና በጉ ግን የታለ?” ሲል ጠየቀ። አብርሃምም “ልጄ ሆይ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ሲል መለሰለት።
ወደ መሥዋዕት ማቅረቢያ ቦታ እንደ ደረሱ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን አስሮ በመሠዊያው ላይ አጋደመው። አብርሃምም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ፤ እግዚአብሔር “ተው በልጁ ላይ ምንም ጉዳት አታድርስበት እንደምትፈራኝና አንድያ ልጅህን ሳስተህ ለኔ እንዳልከለከልከኝ አሁን አውቄአለሁ አለው።
በአቅራቢያው አብርሃም በቊጥቋጦ ውስጥ የታሰረ በግ አየ። እግዚአብሔር በይስሐቅ ፋንታ ለመሥዋዕት የሚሆን በግ አዘጋጅቶ ነበር። አብርሃምም በደስታ በጉን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፣ “አንድያ ልጅህን ሳይቀር ያለህን ሁሉ ልትሰጠኝ ፍቃደኛ ነበርህና ልባርክህ ቃል እገባለሁ። ዘሮችህ ከሰማይ ክዋክብት ይልቅ ይበዛሉ እኔን ስለ ታዘዝከኝ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ባንተ ይባረካሉ።”