unfoldingWord 16 - ነፃ አውጪዎቹ

unfoldingWord 16 - ነፃ አውጪዎቹ

概要: Judges 1-3; 6-8; 1 Samuel 1-10

文本編號: 1216

語言: Amharic

聽眾: General

類型/流派: Bible Stories & Teac

目的: Evangelism; Teaching

聖經摘錄: Paraphrase

狀態: Approved

腳本是翻譯和錄製成其他語言的基本指南,它們需要根據實際需要而進行調整以適合不同的文化和語言。某些使用術語和概念可能需要有更多的解釋,甚至要完全更換或省略。

文本文字

ኢያሱ ከሞተ በኋላ፣ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አልታዘዙም፤ የቀሩትንም ከነዓናውያን ከመካከላቸው አላስወጡም ወይም የእግዚአብሔርን ሕግ አልታዘዙም። እስራኤላውያን እውነተኛ አምላክ የሆነውን ያህዌን ከማምለክ ይልቅ የከነዓናውያንን አማልክት ማምለክ ጀመሩ። እስራኤላውያን ንጉሥ አልነበራቸውም፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ትክክል መስሎ የሚታየውን ሁሉ ያደርግ ነበር።

እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አለመታዘዛቸውን በመቀጠላቸው፣ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን እንዲያጠቁአቸው አደረገ። እነዚህ ጠላቶቻቸው የእስራኤላውያንን እቃዎች ሁሉ ሰረቁ፣ ንብረታቸውንም አወደሙ፣ አብዛኞቻቸውንም ገደሉ። እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝና በጠላቶቻቸው በመጨቆን ብዙ ዘመናትን ካሳለፉ በኋላ፣ ንስሐ ገቡ እግዚአብሔርንም ከጠላቶቻቸው እንዲያድናቸው ጠየቁ።

ከዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶቻቸው የሚያድናቸው ነፃ አውጪ ላከላቸው ለምድሪቱም ሰላምን አመጣ። ነገር ግን ሰዎቹ እግዚአብሔርን እንደ ገና ረሱ። ጣዖትንም ማምለክ ጀመሩ፤ ስለ ሆነም እግዚአብሔር በአቅራቢያቸው የሚገኙትን ጠላቶቻቸውን ምድያማውያንን አስንሣባቸው፣ አሸነፉአቸውም።

ምድያማውያን የእስራኤላውያንን ሰብል ሁሉ ለሰባት ዓመታት ወሰዱ። እስራኤላውያን በጣም ፈርተው ነበር፣ በየሸለቆውና በየዋሻው ተሸሽገው ስለ ነበር ምድያማውያን ሊያገኙአቸው አልቻሉም። በመጨረሻም እንዲያድናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

አንድ ቀን፣ ጌዴዎን የሚባል እስራኤላዊ ምድያማውያን ሰብሉን እንዳይወስዱበት ተደብቆ እህል ይወቃ ነበር። የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ጌዴዎን መጥቶ እንዲህ አለው “አንተ ብርቱ ተዋጊ ሰው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው። ሂድና እስራኤልን ከምድያማውያን አድን።”

የጌዴዎን አባት ለጣዖት አምልኮ የተዘጋጀ መሠዊያ ነበረው። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን ያንን መሠዊያ እንዲያፈርስ ተናገረው። ነገር ግን ጌዴዎን ሕዝቡን ስለ ፈራ እስኪመሽ ድረስ ጠበቀ። ከዚያም መሠዊያውን አፈራረሰው እስኪደቅቅ ድረስም ሰባበረው። በአጠገቡም ለእግዚአብሔር ዐዲስ መሠዊያን አዘጋጀ። ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን ሠዋበት።

በማግስቱ ጠዋት ሕዝቡ አንድ ሰው መሠዊያቸውን እንዳፈራረሰው ተመልክተው እጅግ ተበሳጩ። ጌዴዎንን ለመግደል ወደ ጌዴዎን ቤት ሄዱ። ነገር ግን የጌዴዎን አባት “ለምን አምላካችሁን ለማገዝ ትሞክራላችሁ? እርሱ አምላክ ከሆነ ራሱን ይከላከል!” አላቸው። ይህንንም ስላለ ሕዝቡ ጌዴዎንን አልገደሉትም።

ምድያማውያን አስራኤላውያንን ለመዝረፍ እንደ ገና መጡ። ቊጥራቸው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ማንም ሊቈጥራቸው አይችልም ነበር። ጌዴዎንም ምድያማውያንን ለመውጋት እስራኤላውያንን ጠራ። እግዚአብሔር እርሱን ተጠቅሞ እስራኤልን ያድን እንደ ሆነ ለማረጋገጥ ጌዴዎን ሁለት ምልክቶችን ከእግዚአብሔር ጠየቀ።

ለመጀመሪያው ምልክት ጨርቅ በምድር ላይ አድርጎ የጠዋቱ ጤዛ በጨርቁ ላይ ብቻ እንጂ በምድር ላይ እንዳይሆን ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንደዚያው አደረገ። በሚቀጥለው ምሽት ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፤ መሬቱ በጠዋቱ ጤዛ እንዲረጥብ ጨርቁ ግን ደረቅ ይሁን አለ። እግዚአብሔርም እንደዚያው አደረገ። እነዚህ ሁለቱ ምልክቶች እግዚአብሔር እርሱን ተጠቅሞ እስራኤልን ከምድያም እንደሚያድን ለጌዴዎን ማስረጃ ሆኑለት።

32,000 እስራኤላውያን ወታደሮች ወደ ጌዴዎን መጡ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ቊጥራቸው ብዙ ነው አለው። ስለዚህ ጌዴዎን መዋጋት የፈሩትን 22,000 ወታደሮችን ወደ ቤታቸው መለሳቸው። እግዚአብሔር ጌዴዎንን አሁንም የወታደሩ ቊጥር ብዙ ነው አለው። ስለሆነም ጌዴዎን 300 ወታደሮችን አስቀርቶ ሌሎቹን ወደ ቤታቸው መለሳቸው።

በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ጌዴዎንን “ወደ ምድያማውያን ጦር ሠፈር ውረድ፣ የሚሉትንም ብትሰማ ፈጽመህ አትፍራቸው” አለው። ስለ ሆነም ጌዴዎን ወደ ምድያማውያን ጦር ሠፈር በዚያው ሌሊት ወረደ አንድ የምድያም ወታደር ለጓደኛው በሕልሙ “የጌዴዎን ጦር የምድያምን ጦር ሲያሸንፍ” እንዳየ ሲነገረው ሰማ። ጌዴዎን ይህን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

ከዚያም ጌዴዎን ወደ ወታደሮቹ ተመልሶ ለእያንዳንዳቸው ቀንደ መለከት፣ ማሰሮ እና ችቦ ሰጣቸው። የምድያም ሠራዊት ተኝቶ እያለ ሰፍሮ የነበረበትን የጦር ሠፈር ከበቡ። የጌድዎን 300 ወታደሮች በማሰሮው ውስጥ ችቦ ይዘው ነበር፣ የምድያም ወታደሮች ግን የችቦውን ብርሃን ማየት አልቻሉም።

ከዚያም የጌዴዎን ወታሮች በሙሉ በተመሳሳይ ጊዜ ማሰሮዎቻቸውን ሰበሩ ወዲያው የችቦው ብርሃን በድንገት አበራ። ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሠራዊት” እያሉ ጮኹ።

እግዚአብሔርም ምድያማውያንን ግራ አጋባቸው፣ እርስ በርሳቸውም ተገዳደሉ። ወዲያው በየቤታቸው ያሉ እስራኤላውያን ተጠርተው ምድያማውያንን ለማባረር ተረዳዱ። ብዙዎችን ገደሉ የተቀሩቱንም ከእስራኤል ምድር አባረሩ። በዚያን ጊዜ 120,000 የምድያም ወታደሮች ሞቱ። እግዚአብሔርም እስራኤልን አዳነ።

ሕዝቡም ጌዴዎንን ንጉሣቸው እንዲሆን ፈለጉ። ጌዴዎን ግን ይህን እንዲያደርጉ አልፈቀደላቸውም፤ ነገር ግን እያንዳንዳቸው ከምድያማውያን የወሰዱአቸውን የወርቅ ቀለበት እንዲያመጡ ጠየቃቸው። ሕዝቡም ለጌዴዎን እጅግ ብዙ ወርቅ ሰጡት።

ጌዴዎንም ወርቁን አቅልጦ ሊቀ ካህኑ እንደሚለብሰው ልዩ ልብስ አድርጎ አሠራው። ነገር ግን ሕዝቡ ያንን ልብስ እንደ ጣዖት ሊያመልኩት ጀመሩ። ከዚያም የተነሣ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸው እንዲያሸንፉአቸው አድርጎ ቀጣቸው። በመጨረሻም ሕዝቡ አሁንም እግዚአብሔር እንዲያድናቸው ጠየቁ፣ እግዚአብሔር ሌላ አዳኝ ላከላቸው።

እንዲህ ያለው ሁኔታ ብዙ ጊዜ ተደጋገመ። እስራኤላውያን ኃጢአትን ያደርጋሉ፣ እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል፣ እንደ ገና ንስሐ ይገባሉ፣ እግዚአብሔርም ያድናቸው ዘንድ አዳኝን ይልክላቸዋል። ለብዙ ዓመታት እግዚአብሔር እስራኤልን ለማዳን ብዙ ነፃ አውጪዎችን ልኮላቸዋል።

በመጨረሻም፣ ሕዝቡ ሌሎቹ አሕዛብ እንዳሉአቸው ንጉሥን እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ጠየቁ። በጦርነት የሚመራቸው፣ ረጅምና ጠንካራ የሆነ ንጉሥ እንዲኖራቸው ፈለጉ። እግዚአብሔር ግን ይህንን ጥያቄአቸውን አልወደደም፣ ሆኖም እንደ ፈለጉት ንጉሥን ሰጣቸው።

相關信息

生命之道 - 環球錄音網擁有用數以千計的語言去錄製的福音信息,內容包括一些有關救恩和基督徒樣式的聖經信息。

免費下載 - 免費下載傳教及發展教會組織所用的錄音、圖片、文本和其他相關資料。內容包括聖經故事與傳教課程,并已被翻譯成上千種語言。

環球錄音網音頻圖書館 - 提供mp3,CD和磁帶形式的傳播福音和基本的宣教材料,適宜人們的需要和文化。錄音材料的形式多樣,包括簡單的聖經故事,福音信息,經文朗誦和歌曲。

Choosing the audio or video format to download - What audio and video file formats are available from GRN, and which one is best to use?

Copyright and Licensing - GRN shares it's audio, video and written scripts under Creative Commons